በሴፕቴምበር ወር መጨረሻ በዳታ ሳይንስ እና አናሊቲክስ የስራ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋችን ይስታወሳል። በዚህ ውይይት ብዙዎች እንደተጠቀማችሁ በማመን በዕለቱ በገባነው ቃል መሰረት ክዚህ በታች የሚገኙትን መረጃዎች ልናካፍላችሁ ወደድን።
በውይይቱ ተናጋሪ ለነበሩት መካከል አቤል ይጠቅማሉ ያላቸው መረጃዎች፤
- ለዳታ አናሊቲክስ ወይም ማሽን ለርኒንንግ መደዳደሪያነት የሚያገለግለው ነገር ግን የተለያዩ ለጀማሪዎች የሚሆኑ ስልጠናዎችን በነጻ የሚሰጠው ድህረ–ገፅ –› ኬግል (Kaggle.com)
- የአቤል የሁልጊዜ ምርጥ አጭር ስልጠና ደግሞ የሚሰጠው ዩደሚ (Udemy) በሚባለው ተቋም ነው። ይህም ስልጠና እስከ 10 ዶላር ($10) በሚሆን ክፍያ ልናገኘው እንችላለን። –> Python for Data Science and Machine Learning Bootcam ። መክፈል ለማይችሉ ደግሞ ነፃ የዩደሚ ስልጠናዎችን በየወቅቱ የሚያሳውቀውን ድህረ–ገፅ ይመልከቱ –› Free Udemy cources
- በመጨረሻም አቤል ራሱ የተጠቀመበትን የትምህርት ዕድል አካፍሎናል። ይህም ፕሮግራም በሆላንድ ሀገር በሚገኝ ተቋም የሚስጥ ነፃ የትምህርት እድል ሲሆን፤ ስያሜውም በምህንድስና ፕሮግራም የዳታሳይንስ ሙያዊ ዶክትሬት (Professional Doctorate in Engineering program Data Science) ይባላል። በዚህ ፕሮግራም ለመሰልጠን በመጀመሪያ እነዚህን የማመልከቻ ቅደም ተከተሎችን ይከተሉ። በዚህ የትምህርት እድል የሚያልፉ ተማሪዎች በነጻ መማራቸው ብቻ ሳይሆን ሊከፈላቸውም እንደሚችል አቤል አስረድቶናል።
ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ሌሎችም ትምህርቶች እና ስልጠናዎችን የምናገኝባቸው መንገዶች አሉ።
- በታዋቂው የቴክኖሎጂ ካምፓኒ አይቢኤም (IBM) የሚደገፈው ኮግኒቲቭ ዶት ኤአይ የተሰኘው ድህረገፅ በቢግ ዴታ፣ ዳታ ሳይንስ፣ ዳታ አናሊቲክስ እና የመሳሰሉት መስኮች የተለያዩ ነጻ ስልጠናዎችን በነፃ የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናዎቹን ለሚያጠናቅቁ ደግሞ የምስክር ወረቀቶችን በመስጠት በሊንክዲን እና ሲቪ/ሬዚውሜ (Resume) ላይ ማስቀመጥ ይቻላል። –› cognitive.ai
- ሌላው ጠቃሚ መረጃ ደግሞ በጉግል የሚሰጠው ነጻ ስልጠና ነው። ይህም ስልጠና በራሱ በጉግል የሚሰጥ ሲሆን ፈተናውንም ራሱ ጉግል ፈትኖ ሰርተፊኬት ይሰጣል። –› Google Analytics Academy
ከነዚህ ጠቃሚ መረጃዎች በተጨማሪ ደግሞ መፅሐፍቶችን ማንበብ እና በመስኩ ያሉ የተለያዩ ጸሐፊዎች የከተቧቸውን ልምዶቻቸውን መቅሰም ጥሩ መንገድ ሊሆን ይችላል።
- Data Science from Scratch: First Principles with Python
- Data Science (The MIT Press Essential Knowledge series)
- Python Data Science Handbook: Essential Tools for Working with Data
- Data Science for Business: What You Need to Know About Data Mining and Data-Analytic Thinking
- Data Analytics for Absolute Beginners: A Deconstructed Guide to Data Literacy: (Introduction to Data, Data Visualization, Business Intelligence & Machine Learning)
ከላይ የተዘረዘሩት መረጃዎች እንደጠቀሟቹ እናምናለን። ይህን ደግሞ ለሌሎች በማጋራት እንዲደርሳቸው ያድርጉ። በፖድካስት እና በዩቱዩብ ቻናላችን ላይ ያሉትን በነዚሁ አርዕቶች ላይ የተወያየንበትን ክፍል ይከታተሉ።